10ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መሪዎች

0
620

ምንጭ፡-ሶከር ኢትዮጵያ

ለተከታታይ ሳምንታት በመቐለ 70 እንደርታ ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሪነት ፋሲል ከነማ በሊጉ 25ኛ ሳምንት ጨዋታ እሁድ ግንቦት 11 ቀን በሐዋሳ ከተማ አንድ ለዜሮ በመሸነፍ መሪነቱን ለፋሲል ከነማ አስረክቧል። በተመሳሳይ ሳምንት ፋሲል ከነማ ጅማ አባጅፋርን ስድስት ለአንድ በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ነጥቡን ከፍ ማድረግ ችሏል።

በትግራይ አለማ ዐቀፍ ስታዲየም በተደረው ጨዋታ የበለይነትን ይዞ በነበረው የሐዋሳ ከተማ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ “የሊጉን መሪ በዚህ ሁሉ ሕዝብ ፊት ማሸነፍ የሐዋሳን ጥንካሬ ያሳያል” ሲሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀው ነበር። የመቐለ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ በበኩላቸው “ጨዋታው ለኛ ጥሩ አልነበረም። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በሜዳችን የተሸነፍነው። ጫና ውስጥ ሆነን ስላደረግነው የችኮላ ውሳኔዎች አስቸግረውናል” ሲሉ ገልፀው ነበር።

በ26ኛው ሳምንት ጨዋታዎችም መሪው ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን የሚገጥም ሲሆን በአንድ ነጥብ ርቀት የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ አዳማ ላይ በ30 ነጥብ ርቀት 11ኛ ደረጃ ላይ የሚኘውን አዳማ ከተማን ይገጥማል።

ፋሲል ከነማ በ1960 በጎንደር ከተማ እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ በ1965 መቐለ ላይ መመስረታቸው ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here