የሳኡዲ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን መቀበል አቆመ

0
801

የሳኡዲ አረቢያ መንግሥት በቅርቡ ዜጎቹ ከኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን ማምጣት እንዲችሉ በመፍቀድ በሺዎች የሚቆጠሩ ቪዛዎችን ቢሰጥም ባለፉት ወራት ውስጥ አንድም ሠራተኛ ባለመግባቱ በሩን መዝጋቱን አስታወቀ። ሠራተኞቹ ከረመዳን ጾም በፊት መግባት ነበረባቸው ያለው የአገሪቱ የሠራተኛ እና የማኅበራዊ ዕድገት ባለሥልጣን የቤት ሠራተኞች ምልመላውን ከሌሎች አገሮች ለማካሔድ የሚያስችሉ አማረጮች ላይም ትኩረት ማድረጉ ታውቋል።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተሰጡ የሥራ ቪዛዎችን የሰረዘው ሚኒሰቴሩ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆኑ ያለመግባባቶች በመኖራቸው አገሪቱን ወደ ሳኡዲ አረቢያ መገባት ከሚችሉ አገራት ዝርዝር አውጥተዋል። ያለመስማማቱ በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሠራተኞቹ የሚሆን የጤና ማዕከላትን እንዲከፍት የቀረበለትን ጥያቄ ያለመቀበሉ እንደሆነም የሳኡዲ የዜና አውታሮች ዘግበዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 30 ግንቦት 24 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here