የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ ከኢዜማ ጋር ተቀላቀለ

0
780

የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ (ከሕኮ) ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ጋር መቀላቀሉን ከትላንት በስቲያ ፓርቲዎቹ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ። ፓርቲው ራሱን በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ በምክር ቤትና በጉባኤ ውሳኔዎች በማክሰምና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አስፈላጊ ሰነዶችን በማሟላት ኢዜማን መቀላቀላቸውን አባላቱ አስታውቀዋል።

ከሕኮ ከተመሰረተበት ሐምሌ 23/1983 ጀምሮ በረጅም ዓመታት የፖለቲካ ትግል ውስጥ ያለፈ እንደሆነ እና በተናጠል የሚደረገው ትግል ለድል እንደማያበቃ በመረዳት በአሁኑ ወቅት የፈፀሙት አኩሪ ተግባር ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ነው ሲል አስታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 30 ግንቦት 24 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here