ናይጄሪያ በኢትዮጵያ የሚገኙ 140 ዜጎቿን ለማስፈታት ጥረት እያደረገች ነው

0
356

በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው እና ተፈርዶባቸው በኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ናይጄሪያዊያንን ለመስፈታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የናይጄሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የእስረኛ ልውውጥን ጀምሮ የተለያዩ አማረጮች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ዜጎቻችን እንዲፈቱ እየከርን ነው ያሉት ቃል አቀባዩ የናይጄሪያ ኤምባሲ በተደጋጋሚ እስረኞቹን እንደሚጎነኝም አስታውቀዋል።

አብዛኛውን ጊዜ የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ጋር በተያያዘ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በየኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ክስ እንደሚመሰረትባቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

“የተወሰኑ ናይጄሪያዊን የኢትዮጵያን ሕግ በመጣስ ውስጥ በመሳተፋቸው ያዘንን ሲሆን ኤምባሲያችን ግን ለዜጎች ምሕረት በማድረግ ምህረት ለሚገባቸው ዜጎች ፍትሕ እንዲሰጥ ጠንክሮ ይሰራል” በማለት ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይም በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ በሚካሔደው የኢትዮ-ናይጄሪያ ጉባኤ ላይ በኹለቱ አገራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ እንደሚመክሩ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 30 ግንቦት 24 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here