ኢትዮጵያ ሶማሊያን ይቅርታ ጠየቀች

0
358

የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በድረ ገጽ ላይ የሶማሊያን ካርታ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ግዛት ጋር ቀይጦ፣ ሶማሊ ላንድን ብቻ እንደ ነፃ ሐገር የሚያሳየውን የተሳሳተ ካርታ ተለጥፎ በመገኘቱ ይቅርታ ጠየቀ። ሚንስቴሩ በሳምንቱ ማብቂያ ስህተቱ በተሰራበት ድረ ገጹ ላይ ባስተላለፈው የይቅርታ መልዕክት ካርታው በስህተት የተለጠፈ እንደሆነ እና ስህተቱ እንደታወቀም ወዲውኑ መነሳቱን የሚኒስቴሩ ቃል አቃባይ ነቢያት ጌታቸዉ ገልፀዋል።

ቃል አቀባዩ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ “ጉዳዩን እያጣራን ነዉ ከማለት በስተቀር ጥፋቱን ስላደረሱት ሰዎችና ዓላማቸዉ በግልፅ የተናገሩት ነገር የለም። በየሰበብ አስባቡ ጠብ እና ውዝግብ የማያጣዉ የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግንኙነት ባለፈዉ አንድ ዓመት የወዳጅነት መልክ የያዘ መስሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 30 ግንቦት 24 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here