የባለሥልጣኑ አስተዳደራዊ ችሎት ከ8 ወራት በኋላ ሥራ ጀመረ

0
539

በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ችሎት ብሩህ ግርማ የተባሉ ዳኛ ከሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ሥራ አቁሞ የነበረው ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዳኛ ተሹሞለት ወደ ሥራ መመለሱ ታወቀ።

ለትምህርት ወደ እንግሊዝ አገር የሔዱትን ዳኛ በጊዜ ለመተካት ባለመቻሉ እና የአስተዳደራዊ ችሎቱም ከሦስት ዳኛ ባነሰ መታይት የማይቻል በመሆኑ ችሎቱ ጉዳዮችን ለማየት አለመቻሉን ገለፆ ነበር።

የባለሥልጣኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ከሦስት በላይ ዳኛ እንዲቀጠር የማይፈቅድ ሲሆን ረዳት ዳኞችን የመቅጠርም መብት ስለሌለው አንድ ደና ከለቀቀ እስከሚሾም ባለው ክፍተት ችሎቱ ሥራ ቆማል። የአምቦ ውሃን እና የኮካ ኮላን የውሕዳት ክስ ጨምሮ ትልልቅ እና በተለይም ኢፍታሓዊ ለሆኑ የገበያ ውድድሮችን ለማስወገድ ጊዜ ሳይሰጣቸው ታይተው ማለቅ የነበረባቸው ክሶች መጓተታቸውን እና ይህም አሉታዊ ውጤት ማስከተሉን የባለሥለጣኑን ሠራተኞች ይገልፃሉ።

ዳኞቹ የዓመት ፈቃድ የማይወጡ ሲሆን ሕመም በሚያጋጥማቸው ወቅትም ችሎቱ ካለመሰየሙም ባሻገር የሥራ መደራረብ መኖሩም ታውቋል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ ዳይሬክተር ሚካኤል ተክሉ ለወደፊት እንዲህ ዓይነት ችግሮች መከሰት እንደሌለባቸው ገልፀው የባለሥልጣኑ ማቋቋሚያ አዋጅ እየተሸሻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 30 ግንቦት 24 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here