10ቱ ብዙ ሕዝብ የከፋ ድኅነት ውስጥ ያለባቸው የአፍሪካ አገራት

0
331

ምንጭ፡-አይ ኤም ኤፍ 2019 (እ.ኤ.አ.)

ያለፈው ዓመት ዓለም በታሪኳ ዝቅተኛ የሚበል የከፋ ድኅነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር ያሰመዘገበችበት እንደነበር የወርልድ ባንክ ሪፖርት ያሳያል። ነገር ግን 68.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉብት ዓመት በመሆኑ ይህ ስኬት ላይ የራሱን ጥላ ማጥለቱንም ባንኩ ይጠቁማል።

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ከዚህ እውነታ ርቀው እና የከፋ ድኅነት ውስጥ ዜጎቻቸው የገቡበት እና ቁጥሩም የጨመረበት መጨመሩን ቀጥሎ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያም ከሕንድ ዓለማቀፍ መሪነቱን ተቀብላ ቁንጮ ላይ ለመቀጥም ቀርባለች።

ከዓለማችን ሕዝብ አንድ ቢሊዮን የሚሆኑት ባለፈው ሰላሳ ዓመት በቀን ወደ ኹለት ዶላር ገደማ ገቢ በማግኘት ራሳቸውን ከከፋ ድኅነት ለማለቀቅ ችለዋል።

የአየር ንብረት ለውጦችን ለመቋቋም በማትችልበት ደረጃ ላይ በመድረስ ላይ ያለችው ዓለም የድኅነት ቅነሳ ፍጥነት ከነበረበት መውረድ መጀመሩን ተከትሎ ችግሩን የወደፊቱ የድኅነት ቅነሳ ሥራ አሳሳቢ መሆኑን ወርልድ ባንክ ይተነትናል።
በዓለማችን አሁንም 736 መቶ ሚሊዮን ሕዝቦች አሁንም ከድኅነት ወለል በታች ይኖራሉ።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here