በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺሕ በላይ ቀነሰ

0
829

ባለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ወራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ ምክንያት የ4 ሺሕ 10 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከፌደራል ፖለስ በሰበሰበው መረጃ መሰረት የአማራ ክልል በ32 ነጠብ 9 በመቶ ከፍተኛ የሆነውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን ኦሮሚያ 30 ነጥብ 5 በመቶ፣ ደቡብ 13 ነጥብ 5 በመቶ ፣ አዲስ አበባ 9 ነጥብ 2 በመቶ እና ትግራይ 7 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነውን የሞት አደጋ ማስተናገዳቸውም ተገልጿል።

ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ዋነኛ መንስኤዎችም የሰዎች ሥነ ባሕሪይ፣ የመንገድ ዲዛይንና አካባቢ እና የተሸከርካሪ ቴክኒክ ችግር መሆናቸውን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የመንገድ ትራፊክ አደጋን አስመልክቶ የወጣው መረጃ ያሳያል። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት ገለፃ በየዓመቱ 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን በታዳጊ አገራት በየዓመቱ ከ600 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ንብረት በአደጋው ይወድማል። ይህም ከዓመታዊ ምርታቸው ላይ ከ1 እስከ 3 በመቶ እንደሚያጡ ያሳያል።

ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here