ከሰኔ 30 ጀምሮ በሞተር ሳይክል መጓጓዝ ተከለከለ

0
642

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 30/2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሞተር ሳይክልን ለመጓጓዣነት መጠቀም እንደሚከለክል አስታውቋል። አስተዳደሩ እንዳስታወቀው በከተማዋ እየተበራከተ የመጣውን በሞተር ሳይክል የታገዘ ስርቆትና ዝርፊያ ወንጀሎች ለመከላከል የታሰበ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የትራፊክ አደጋውንም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንሰው አስረድቷል። የአስተዳደሩ መግለጫ እንደሚያመለክተው በከተማዋ በስርቆት ወንጀል ተሳትፈው የተያዙ ሞተር ሳይክሎች በአብዛኛው የክልል ሰሌዳ የለጠፉ መሆናቸውንም ገልጿል።

አስተዳደሩ በመግለጫው በተሰጠው ጊዜ ገደብ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2011 ድረስ የሞተር ሳይክል ባለንብረቶች ሞተር ሳይክሎችን እንዲሰበስቡም አስታውቋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፖስታ ቤት እና ሌሎች የዓለም ዐቀፍ የዲፕሎማሲ መሥሪያ ቤቶች ከትራንስፖርት ባለሥልጣን ፈቃድ በማግኘት ሞተር ሳይክሎችን መጠቀም እንደሚችሉ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here