የግብጽ ዓለም ዐቀፍ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ቢሮውን ሊከፍት ነው

0
584

በሰኔ ወር መጨረሻ የግብጹ ዓለም ዐቀፍ ንግድ ባንክ (ሲአይቢ) በኢትዮጵያ ቢሮውን እንደሚከፍት አስታወቀ። የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንዳስታወቁት ባንኩ በቅርቡ በአፍሪካ ያለውን አዲስ የባንክ አሰራር የጀመረ ሲሆን ይህም በበርካታ አፍካዊ አገራት ቅርንጫፍ ቢሮዎችን እንዲከፍት እንዳስቻለው ተናግረዋል ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ባንኩ በ41 የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ቢሮዎችና የገንዘብ ተቋማትን ማቋቋሙ ታውቋል። ዋና መቀመጫውን በግብፅ ካይሮ ያደረገው እና በግል ሴክተር የተቋቋመው ባንኩ፣ በአሁኑ ወቅት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ወደ 6 ሺሕ ገደማ የሚደርሱ ሠራተኞች እንዳሉት መረጃዎች ያመላክታሉ። ባንኩ ጠቅላላ ሀብቱም 263 ነጥብ 8 ቢሊዮን የግብፅ ፓውንድ እንደሆነም ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 35 ሰኔ 29 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here