10ቱ የፆታ እኩልነት ክፍተትን መጥበብ የቻሉ አገራት

0
540

ምንጭ: የአለም የኢኮኖሚ ፎረም እ.ኤ.ኣ 2018

የአለም የኢኮኖሚ ፎረም በየአመቱ ከተለያዩ ሃገራት በሚሰበሰብሰው መረጃ ላይ ተመስርቶ በተለይም በኢኮኖሚ ተሳትፎ እና እድል፣ የትምርሀርት እድል፣ ጤና እና የእድሜ ጣሪያ እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሃገራት በወንዶች እና በሴቶች ዜጎቻቸው መካከል ያለውን የእኩልነት መጠን ይለካሉ፡፡

በእነዚህ መለኪያዎች ላይ በመመስረት በሚወጣው የክፍተት ምጣኔም ወደ አንድ የተጠጉ ሃገራት የተሸለ መሻሻል ያሳዩ ሲሆኑ ኢትዮጲያን ጨምሮ ዝቅተኛ ውጤት ያሳዩ ሃገራት ከአንድ ያራቀ ውጤት ያስመዘግባሉ፡፡

አውሮፓዊያኑ ሃገራት ከፍተኛ መሻሻል በማሳየት የፆታ እኩልነት ክፍትቱን ማጥበብ የቻሉ ሲሆን የአፍሪካ እና የአረብ ሃገራት ዝቅተኛውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ኢትዮጲያም 0.656 በማስመዝገብ 117ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን የመን 0.499 በማስመዝገብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች፡፡ ከአፍሪካ ሃገራት ውስጥም ሩዋንዳ ከፍተኛ የሚባል ውጤትን በማስመዝገብ በ51 ደረጃ ላይ የተቀመጥችውን አሜሪካን ጨምሮ ፈረሳይን፣ ጀርመንን፣ እንግሊዝን እንዲሁም ሌሎች የበለፀጉ ሃገራትን ቀድማ በስድስተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ከፍተና ውጤት አስመዝግባለች፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 35 ሰኔ 29 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here