የአብን ሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ በድጋሚ ታሰሩ

0
790

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሥራ አስፈፃሚ አባል እና የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ክርስቲያን ታደለ ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 በድጋሚ መታሰራቸው ታወቀ። ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከዚህ ቀደም በቁጥር ሥር የዋሉትን የንቅናቄውን አባላት ለመጠየቅ በሔዱበት በሥፍራው በነበሩ የደኅንነት አባላት ተይዘው እንደታሰሩ የአማራ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ዘገባው እንዳስታወቀው ሐምሌ 3 እና 4 በርካታ የአብን አባላት በጸጥታ እና ፍትሕ የጋራ ግብረ ኀይል እየታፈሱ መታሰራቸውን ገልጿል። የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ከሦስት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለኹለተኛ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል። ክርስቲያን ከዚህ ቀደም በባሕር ዳርና በአዲስ አበባ ባለሥልጣናት ላይ የተሰነዘረውን ግድያ ተከትሎ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ማንኩሳ ወረዳ ለሥራ በሔዱበት በቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ቀን በኋላ ተፈትተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 36 ሐምሌ 6 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here