ዛይ ራይድ ለ200 ሴቶች ታክሲ ገዝቶ ሊሰጥ ነው

0
1886

በአዲስ አበባ የታክሲ ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ከሚሰጡት ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዛይ ራይድ 200 መቶ ሴቶች ከባንክ ብድር በማመቻቸት ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎችን ገዝቶ ሊሰጥ እንደሆነ አስታወቀ። ኩባንያው ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመነጋገር ሰርተው መለወጥ ለሚፈልጉ ሴት አሽከርካሪዎች የመኪኖችን ዋጋ 70 በመቶ የአቢሲኒያ ባንክ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪውን 30 በመቶ ደግሞ ሴቶች በረጅም ጊዜ ክፍያ ቆጥበው እንደሚከፍሉ ታውቋል።

ኩባንያው ለማስገባት ያቀዳቸውን ሜትር ታክሲዎች ከጣሊያን የመኪና አምራች ኩባንያ ፊያት ጋርም ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የመጓጓዣ እጥረት ለመቅረፍ ወደ ሥራ የገባው ዛይ ራይድ ሦስት ዓመታትን በሥራ ላይ ማሳለፉ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም ወደ ምዕራብ አፍሪካ በመሻገር ሥራ ሊጀምር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ይህንም ተከትሎ በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞኖሮቪያ እና በጊኒ ኮናክሪ የአገልግሎት አድማሱን ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ማለዳ ሐምሌ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here