ቴዲ አፍሮ እና ደራርቱ ቱሉ በአሜሪካ ተሸለሙ

0
1031

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ መሸለማቸው ታወቀ። ሐምሌ 13/2011 በዋሽንግተን ዲሲ የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ቴዎድሮስ ካሳሁንን በአፍሪካ ወጣቶች ላይ ላበረከተው መልካም አርዓያነት የዕውቅና ሽልማት ሰጥቶታል። በዚሁ ወቅትም የጽሕፈት ቤቱ ዋና ተጠሪ ኤሪካ ዶንቦሪኮ (ዶ/ር) ቴዲ አፍሮ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ወጣቶች ላይ ጉልህ ሚና መጫወቱን በማንሳት ሽልማቱ በእርግጥ የሚገባው ነው ሲሉም አረጋግጠዋል። ከኹለት ሳምንታት በፊት በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ለቴዲ አፍሮ የዕውቅና ሽልማት መስጠታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተመሳሳይም በዋሽንግተን ዲሲ አትሌት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉም ከዋሽንግተን ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የዕውቅና ሽልማት ተችሯታል። በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት በሚል የከንቲባ ጽሕፈት ቤቱ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷታል።

የኹለቱን ተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያኖችን ሽልማት ዝግጅት የመሩት በሰሜን አሜሪካ የታላቁ አፍሪካ ሩጫ ውድድር ዋና አዘጋጅ ጋሻው አበዛ (ዶ/ር) ናቸው።

አዲስ ማለዳ ሐምሌ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here