10ቱ የግብርና አስተዋጽዖ ከጥቅል አገራዊ ምርት አንጻር

0
626

ምንጭ: ብሪቱ መጽሔት የሚያዚያ 2011 ዕትም

ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ 80 በመቶ ለሚሆነው ሕዝብ ኑሮ መሰረት የሆነው የግብርናው ዘርፍ ከአነስተኛ ግብርና መላቀቅ ባለመቻሉ የሚፈለገውን ያህል የኢኮኖሚ ሚና መጫወት እንዳልቻለ የተለዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

እንደ ዓለም ዐቀፉ የምግብ ድርጅት (‘ፋኦ’) አነስተኛ ግብርና ማለት አንድ ገበሬ ከአንድ ሔክታር እስከ 10 ሔክታር መሬት ላይ የግብርና ሥራውን የሚያከናውን ሲሆን እና የግብርናው ውጤት ለገበሬው እና ለቤተሰቦቹ ፍጆታ ከመሆን ባለፈ ለገበያ ቀርቦ ትርፍ የማያስገኝ ሲሆን ነው።

በኢትዮጵያም ለተከታታይ ዓመታት ሲጨምር የቆየው የግብርናው ድርሻ ለጥቅል አገራዊ ምርቱ ላለፉት ዐሥር ዓመታት በመቀነስ በ2001 ከነበረበት የ47.3 በመቶ ድርሻ ወደ 34.9 መውረዱን የፕላን ኮሚሽን ሪፖርት ያሳያል። ይህም በዋናነት መንግሥት የአገልግሎት ዘርፉ እንዲያድግ ባደረጋቸው ጥረቶች ምክንያት የግብርናው ምርታማነት ቢጨምርም ከጥቅል አገራዊ ምርቱ አንጻር ያለው ድርሻ ግን በአገልግሎቱ በከፍተኛ ዕድገት ምክንያት መቀነሱን ይናገራሉ።

አዲስ ማለዳ ሐምሌ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here