በአፋር ክልል በተነሳ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ ሰዎች ቆሰሉ

0
337

ሐምሌ 24/2011 በአፋር ክልል በአሳኢታ ከተማ በተነሳ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 5 ሰዎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ንፋሱ “ቦራውሊ” የሚባለው የስደተኞች ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ቤቶች መፍረሳቸውም ታውቋል።

በተገለፀው የስደተኞች መጠለያ ስፍራ የሚገኙት አብዛኞቹ የኤርትራ ስደተኞች ሲሆኑ፣ መጠለያቸው መውደሙን፤ ከዕርዳታ ድርጅቶች የተሰጣቸው ምግብም የተወሰነው መበላሸቱን ገልጸዋል። በዚህ ስፍራ ወደ 7 ሺሕ የሚገመቱ ተፈናቃዮች መጠለላቸው ነው የተነገረው። መኖሪያ እና መጠለያቸው ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ እና የሚመገቡትም በመበላሸቱ በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።

እንደዚህ ዓይነት አውሎ ንፋስ በአካባቢው በዓመት እና በኹለት ዓመት እየተከሰተ በርካታ ውድመቶችን በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ አድርሶ እንደሚያልፍ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 39 ሐምሌ 27 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here