ብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ 850 ሚሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ

0
540

የብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ በ2011 በጀት ዓመት ካመረታቸው 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር አልኮል መጠጦች እና 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሊትር ንፁሕ አልኮል 850 ሚሊዮን ብር ማግኘቱን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። ፋብሪካው በ2011 በጀት ዓመት ያገነው ገቢ አሳካዋለሁ ብሎ ከተነሳው 750 ሚሊዮን ብር ዕቅዱን 107 በመቶ በማሳካት 850 ሚሊዮን ብር ለማግኘት እንደቻለ ታውቋል።

የኤጀንሲው በሥሩ ያሉትን የልማት ድርጅቶች የ2011 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም እና የቀጣዩን ዓመት ማለትም 2012 ዕቅድ ዝግጅት ሐምሌ 24 በገመገመበት ወቅት ብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ በዕቅዱ መሰረት 200 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ለማግኘት ታስቦ የነበረ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ እንደተገለፀው ግን 233 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ማግኘቱን ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 39 ሐምሌ 27 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here