1 ሺሕ 5 መቶ ሔክታር መሬት ለአልሚዎች ሊሰጥ ነው

0
458

በአዲስ አበባ ከተማ 1 ሺሕ 5 መቶ ሔክታር መሬት በግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ሊሰጥ እንደሆነ ታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የ2011 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደገለፁት የከተማዋ ነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል አዲስ የቤት ልማት መርሃ ግብር ለመጀመር 1 ሺሕ 500 ሔክታር መሬት የተዘጋጀ ሲሆን የግሉ ዘርፍንም ለማሳተፍ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል።

ምክትል ከንቲባው በሪፖርታቸው አያይዘው እንደገለፁት መልማት ያልቻሉ ሰፋፊ መሬቶችን በመንግሥትም ይሁን በግለሰቦች ተይዘው የቆዩ ጥናት ተደርጎባቸው ወደ መሬት ባንክ እንደተላለፉ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል።

በሌላ በኩልም ደግሞ ከተማዋ አስተዳደር ባካሔደው ሰፊ ንቅናቄ ከ10 ሺሕ በላይ ወጣቶችን ከጎዳና ለማንሳት እንደተቻለ ምክትል ከንቲባው አስታውቀዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 39 ሐምሌ 27 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here