የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ልደት ነሐሴ 12/2011 ይከበራል

0
789

የየዳግማዊ አፄ ምኒልክ የልደት በዓል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መናገሻ ባህር ዳር ከተማ እሁድ ነሐሴ 12 2011 እንደሚከበር ታውቋል፡፡ የክልሉ የቱሪዝም ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልካሙ አዳሙ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት በዓሉ ከዚህ በፊት ፍላጎቱ ባላቸዉ ወጣቶች ተነሳሽነት ከ2008 እስከ 2010 መከበሩን አስታዉሰዉ በያዝነዉ ዓመት ግን መንግሥታዊ ዕውቅና ተችሮት የቱሪዝም ልማት ቢሮ በዋናነት እንደሚያዘጋጀው ገልፀዋል፡፡

ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ከአባታቸዉ ኃይለ መለኮት እና ከእናታቸዉ እጅጋየሁ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንቁላል ኮሶ በሚባል ቦታ ነሐሴ 12/1836 እንደተወለዱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

በ175ኛው የአፄ ምኒልክ ልደት በዓል ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን፥ በአፄ ምኒልክ አስተዳደር ወቅት በህግ በኩል ያደረጓቸዉን አስተዋፅኦዎች፤ በታሪክ ዉስጥ ያላቸዉን ቦታ እና ባደረጓቸዉ ዘመቻዎች የነበረዉ ሂደት ያካተቱ ናቸው፡፡ ግጥምና መነባንቦች የበዓሉ ዝግጅት አካል ናቸዉ፡፡

በዓሉ በክልሉ ተምሳሌት የሆኑ ሰዎችን የማመስገን እና የማክበር ዓላማን የያዘ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክልሉን ባህላዊ እሴቶችን ይዳሰሳሉ፡፡ በተጨማሪም በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ዙሪያ የተለያዩና አሳማኝ ያልሆኑ ትንታኔዎች በመኖራቸዉ ታሪካዊ መረጃን መሰረት አድርጎ ስህተትን ለማረም ታስቧል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here