የገቢዎች ሚኒስቴር 20.6 ቢሊየን ብር ውዝፍ ዕዳ ሰበሰበ

0
550

የገቢዎች ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ግዜ ከአዲስ አበባ ውጪ ካሉ ሰባት ቅርንጫፎቹ የግብር ዕዳ መረጃን ላይ ተመርኩዞ 20.6 ቢሊዮን ብር ያህሉን መሰብሰቡን ተናግሯል፤ ይህም ከእቅዱ አራት ቢሊዮን ብር በላይ ከመሆኑም ባሻገር ከአጠቃላይ ገቢው 17 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
እንደሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገለጻ፥ ባለፈው የ2011 የበጀት ዓመትም 58 ቢሊዮን ብር ሳይሰበሰብ ወደተያዘው የ2012 የበጀት ዓመት የተዘዋወረ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 32 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በተለያዩ የአቤቱታ እርከኖች ላይ እንደሚገኝ ተገለጿል። በተጨማሪም 25 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ታክስ ውዝፍ ዕዳ ወደተያዘው ዓመት ተላልፏል።

“በሕግ ማስከበር ሒደቱ ከፍተኛ ግብር ዕዳ ተሰብስቧል” ያለው ሚኒስቴሩ ወደ ተያዘው በጀት ዓመትም ከተዘዋወረው ዕዳ ውስጥ 13 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በተጣለ ዕግድ ነው ሲል ገልጿል።

ካለፈው በጀት ዓመት የዞሩትን አቤቱታዎች ጨምሮ በዋና መሥሪያ ቤቱ የይግባኝ ሰሚ የቀረቡ አቤቱታዎች አንድ ሺሕ ኹለት መቶ በላይ አቤቱታዎች የቀረቡ ሲሆን፥ ከ23ቱ ውጪ እልባት ማግኘታቸውም ተጠቅሷል። ውሳኔ ከተሰጠባቸው እነዚህ መዝገቦች ውስጥ አራት ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነው ለሚኒስቴሩ የተፈረደ ሲሆን፥ ከአንድ ቢሊዮን ብር ያነሰው ደግሞ ለግብር ከፋዮች የተፈረደ ነው። በአንድ ዓመት ውስጥ ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይም ተመላሽ መደረጉ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here