በመዲናዋ በአንድ አመት ውስጥ 115ሺህ የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጠ

0
509
  • በ25 ከተሞች የወሰን ቅየሳ ተካሂዷል

በ2010 የበጀት አመት በመላው ሃገሪቱ ከተሰጡ የይዞታ ማረጋገጫዎች ውስጥ ከ 88 በመቶ በላይ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ እንደሆነ የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በመላው ኢትዮጲያ ባሉ 23 ከተሞች ከተሰጡ 130 ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሶስት ማረጋገጫዎች ውስጥ 115 ሺህ አንድ መቶ አራት የሚሆኑት በመዲናዋ የተሰጡ መሆናቸውም ታውቋል።

በበጀት ዓመቱም ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የይዞታ ማረጋገጥ ስራ የተሰራባቸው ክልሎች መሆናቸውንም የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአሥሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 167 ቀጠናዎች እና 749 የሠፈር አካባቢዎች የይዞታ ማረጋገጫ ማካናወኛ ካርታዎች ከማዘጋጀቱም ባለፈ 136 ሺህ በላይ የሚሆኑ የቁራሽ መሬቶች ልዩ ኮድ ሰጥቷል፡፡ሆኖም ለቁራሽ መሬቶቹ የተሰጠውን ልዩ ኮድ ከይዞታ ማህደሮች ጋር እንዲተሳሰሩም መደረጉ ታውቋል።

በተጨማሪም በ25 ከተሞች የወሰን ቅየሳ መደረጉን ያስታወቀው ኤጀንሲው በነዚህ ከተሞች ከ23 ሺህ በላይ ይዞታዎች ላይ የአየር ካርታን ያቀናጀ ቅየሳ በማድረግ ለይዞታ ማረጋገጥ ተግባር ዝግጁ የማድረግ ስራ እንደተሰራም አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለካዳስተር ቅየሳ መሳሪያዎች መለክያ የሚሆኑ የማመሳከርያ ተከላዎችን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር ፤ ህንፃ ግንባታ እና ከተማ ልማት የሚከናውን ይሆናል።

የወሰን ቅየሳ በሚሰራበት ግዜ የማመሳከርያ ተከላዎቹ በግዜው የተጠናቀቁ ቢሆኑም የቅየሳ መሳርያዎችን የጥራት መጠን ለመወሰን የሚያስችል አልነበረም፡፡ እንዲሁም በተሻለ መልኩ የቅየሳ መሳሪያ ተገዝቶ ባለመገጠሙ ምክንያት እንደሆነ ሪፖርቱ አመላክቷል። በቀጣይም ይህን አሰራር በመቀየር የተሸለ ስራን ለማከናወን ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው ሲሉ በከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ባለሞያ የሆኑት ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here