የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ኤፍ ቢ አይ መረጃ ለመለዋወጥ ተስማሙ

0
392

የብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ገብረሚካኤል እና የአሜሪካው የምርመራ ቢሮ ኤፍ.ቢ.አይ ምክትል ዳይሬክተር ቻርልስ ኬብል ኹለቱ ሃገራት የሽብርተኞችን መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

በኢትዮጲያ የአሜሪካን ኤምባሲ እንዳስታወቀው ነሐሴ 14/2011 በተደረገው ስምምነት በኹለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ ስርአት የሚያበጅ እና ኹለቱም ሃገራት ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያግዛቸው እንደሚሆንም ተገልጿል።

‹‹ስምምነቱ ኹለቱ ሃገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ሽብርተኝነት ለመከላከል ያግዛል እንዲሁም የሃገራቱን ደኅንነት ያረጋግጣል›› ኤምባሲው ገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here