ዓረናና ትዴት በአገሪቱ አፈና እየተፈጸም ነው አሉ

0
696

በትግራይ ‘አፈና እየተፈፀመ’ ነው፣ አመራሮቻችንና አባላቶቻችን ላይ የግድያ ሙከራን ጨምሮ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ነው ሲሉ ዓረና ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ (አረና) እና የትግራይ ዴሞክራስያዊ ትብብር (ትዴት) ፓርቲዎች ሃሙስ 23/2011 በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ፡፡

ሕገ መንግሥት ይከበር በሚባልበት ወቅት ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ነው ያሉት የአረና ሊቀ መንበር አብርሃ ደስታ፣ ሕገ መንግሥቱ የሰጠንን የመንቀሳቀስ መብት ተነፍገን እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመላ ሀገሪቱ አፈና እየተፈፀመ መሆኑን ያወሱት አብርሃ፣ አፈናው ተጠናክሮ የሚገኘው በትግራይ እንደሆነም አክለዋል፡፡ የትዴት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሙሉብርሃን ኃይለ በበኩላቸው፣ ባለፈው ሳምንት “ሕገ መንግሥቱንና የፌደራል ስርዓቱን ማዳን” በሚል በመቐለ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በትግራይ ያሉ የፖለቲካ ሀይሎች አለመገኘታቸው በትግራይ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ምርጫው መካሄድ ያለበት የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍቶ መሆን እንዳለበትም በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here