ዳሰሳ ዘ ማለዳ አርብ ነሐሴ 24/2011

0
873
  • አዲስ አበባ የሚገኘው የሮያል ዴንማርክ ኢምባሲ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት የሚያስችል ፕሮጀክት ለመጀመር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ጀምሯል።በውይይቱ የሰላም ሚንስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፋይናንስ ደኅንነት ማዕከል ተሳታፊ ሆነዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………..

  • የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ዛሬ ነሐሴ 24/2011 ለሰባት ድርጅቶች የማዕድን ምርመራ እና ለሦስት ድርጅቶች ደግሞ የማዕድን ምርት ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል። ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በደቡብ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ብሔራዊ ክልሎች በማዕድን ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

  • ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር በዋሉት የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ቴዎድሮስ ገቢባ ምትክ ጥራቱ በየነን የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት ከተማዋን በምክትል ከንቲባነት እንዲመሩ መርጧል (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

  • በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ።(ዋልታ)

…………………………………………………..

  • የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ከሰኞ ነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜ 2/2011 በሒልተን ሆቴል ይካሔዳል። በማጠቃለያው ላይ ጠቅላይ ሚንስቴር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ለስራ ኃላፊዎች እና አምባሳደሮች የስራ መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

…………………………………………………..

  • የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ኮርፖሬሽኑ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡(አብመድ)

………………………………………..

  • ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ድንበር በኩል አቋርጠው ወደ ደበብ አፍሪካና፣ ታንዛኒያ እንዲሁም ወደ ሌሎች አገሮች ለመሔድ ሲሉ ለጉዳት እየተዳረጉ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………

በአዲስ አበባ ተገንብተው ለመጠናቀቅ የኹለት ዓመታት ጊዜ ተይዞላቸው የነበሩ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሰባት ዓመታትን ቢያስቆጥሩም ግንባታቸው አልተጠናቀቀም ተባለ። (ዶቼ ቬለ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here