ምርጫ ቦርድ የሲዳማን ህዝበ ውሳኔን ለማካሄድ ከነሃሴ 30/2011 ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ሳምንታት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል። ለምርጫውም ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንደሚመለምልና አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎችን እንደሚያደራጅ ገልጿል። የህዝበ ውሳኔ መመሪያዎች የማውጣትና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመት የመሳሰሉትን ስራዎች እንደሚያከናውንም ቦርዱ በጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቋል።
ቦርዱ በተጨማሪም ከመስከረም 07/2012 ጀምሮ የህዝበ ውሳኔውን ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ የእቅድ ዝግጅት ለማከናወን ከፌደራል፣ ከክልል እና ከዞን የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ የማውጣት ውይይቶችን ያደርጋል።
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሀዋሳን ከተማ የወደፊት ሁኔታ ፤የሀብት ክፍፍል እና የሌሎች ብሄረሰብ አባላትን የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎችን ማውጣት ስራ እስከ መስከረም 22 ድረስ ያጠናቅቃል ተብሏል፡፡
ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011



