ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው በነበሩ ኹለት ስዊድናዊያን ዙሪያ ፊልም ተሰራ

0
1279

በኢትዮጵያ ውስጥ በ2003 ከሱማሊያ አሸባሪ ቡድን ጋር አብረው ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተዋግተዋል በሚል ቆስለው በተያዙት ኹለት ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ እንግሊዘኛ ፊልም ተሰርቷል። ማርቲን ሺቤይ እና ጆን ፔርሰን የተባሉት ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች በ2003 በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት አስራ አንድ ዓመታት እስር ተፈርዶባቸው ወደ ዘብጥያ ወርደው እንደነበር የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ከአስራ አምስት ወራት በኋላ በምህረት ከኢትዮጵያ እስር ቤት ወጥተው ወደ አገራቸው ስዊድን አቅንተዋል።

‹‹438›› የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ፊልም ኹለቱ ጋዜጠኞች በጠቅላላ በእስር ያሳለፉትን ቀናት ለመግለፅ የተሰጠው ስያሜ ሲሆን ፊልሙም ጋዜጠኞቹ በኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጀምሮ፣ ፍርድ ቤት ውሏቸው እና በእስር ቤት የነበራቸውን ቆይታ በሰፊው እንደሚያሳይ ተነግሯል። የፊልሙ ደራሲ ፒተር ቢሮ ሲሆን በ2005 በኹለቱ ጋዜጠኞች ዙሪያ ከተፃፈው መጻሕፍ የተወሰደ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here