ከጳጉሜ 1 እስከ 6 ለ1 ሺሕ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል

0
537

በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ከጳጉሜ 1 እስከ 6/2011 ”ጳጉሜን ለጤና” በሚል መሪ ቃል ለ1 ሽሕ ሰዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል። በውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል የሚሰጠው ነፃ የምርመራና የሕክምና አገልግሎት አጠቃላይ የውስጥ ደዌን ጨምሮ የአንገት ፣ የጉበት፣ የካንሰር፣ የጨጓራ፣ የልብና ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳዊት ኃይሉ የማእከሉን አስረኛ ዓመት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ክብረ በዓሉን በበጎ አድራጎት እንደሚያከብሩ እና ለ1 ሽሕ ዜጎች ነፃ ምርመራና ሕክምና መስጠት አንደኛው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴው አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። ዳዊት አያይዘውም በማዕከሉ ከፍለው መታከም ለማይችሉ እና ከዚህ ቀደም ተመርምረው የሐኪም ማዘዣ ያላቸው ግለሰቦች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቀድመው መመዝገብ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። ውዳሴ ዲያግኖስቲክ በኢትዮጵያ በውስጥ ደዌ እና አጥንት ሕክምና ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ማዕከል ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here