የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የሙያ ስነ ምግባር ጉድለት እየታየባቸው ነው ተባለ

0
381

ሐሙስ ነሐሴ 23/2011 “የሀገራችን የሚዲያ ተቋማትና የሚሰጡት አገልግሎት በህዝብ እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ ያገኙትን አንጻራዊ ነጻነት ተከትሎ የሙያ ስነምግባር ጉድለቶች እና ገለልተኛ ያለመሆን ችግር እየተስተዋለባቸው ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አልማዝ መኮንን ተናገሩ።

በመድረኩ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ በበኩላቸው፣ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የእውቀት፣ የባህልና ቋንቋ አጠቃቀም ክፍተት አለባቸው ብለዋል። ማህበረሰብን የማገልገል ግባቸውን የሚረሱ ሚዲያዎች እንዳሉም ጠቁመዋል። የሀገሪቱ ጋዜጠኞች በልምድ፣ በሙያ የሚሰሩና አብዛኞቹ ያለ ልምድ ከውጪ የተኮረጁ ፕሮግራሞችን ብቻ የሚያቀርቡ ሲሉም በኹለት ከፍለዋቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር)፣ “ፕሮግራም አዘጋጆች ከማስታወቂያ ገቢ ምን ያህል አገኛለሁ” ከማለት በኅብረተሰቡ በሚያመጡት ለውጥ ራሳቸውን ሊለኩት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here