አዲስ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ አጀንዳ ይፋ ሆነ

0
311

በኢትዮጵያ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት የታየውን ለውጥ ለማስቀጠልና አገሪቱን ወደ ተሻለ ምጣኔ ሀብት ደረጃ ለማሸጋገር ይረዳል የተባለው አዲስ አጀንዳ ረቡዕ ነሐሴ 22/2011 ይፋ ሆኗል። አጀንዳው በዋናነት አገር በቀል ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እንደሆነና ለወጣቶች ብቁ የሆኑ የሥራ ዕድሎችን መዘርጋትና ኹሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ምጣኔ ሀብት መገንባት እንደሆነም አጀንዳው ይፋ በሆነበት ወቅት ታውቋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ መቀዛቀዞች መታየታቸውን እና የወጪ ንግዱም ላይ ጥላ ማጥላቱን ምክንያት በማድረግ ውጭ ምንዛሪ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ተናግረዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ የተገኙ ሲሆን፣ ስለ መርሃ ግብሩ አካሔድ መግለጫ ሰጥተዋል። መርሃ ግብሩን በዋናነት የገንዘብ ሚኒስቴር የሚያስተባብረው ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስቴር የሚመራ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር የበላይ ኮሚቴ የሚከናወን እንደሚሆን አስታውቀዋል ።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here