ቱርክ በተመረጡ 17 አገራት ላይ የወጪ ንግዷን በእጥፍ ለመጨመር ማቀዷን ይፋ አደረገች

0
384

ቱርክ ለዓለም ገበያ ምታቀርባቸውን ምርቶች በተመረጡ 17 አገራት ላይ በአምስት ዘርፍ የምትልካቸውን ምርቶች እጥፍ ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋለች። ከተመረጡት አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካን እና ኬንያን ጨምሮ ሦስት አገራት መሆናቸው ታውቋል።

ቱርክ የወጪ ንግዱን በዕጥፍ ለማድረግ ያለመችው አምስት የተለያዩ ዘርፎች ማሽሪዎችን፣ ተሸከርካሪዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና በኬሚካልና የምግብ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ተጠቃሽ ናቸው። የቱርክ የንግድ ሚኒስትር ሩህሳር ፔካን እንደተናገሩት የተጠቀሰሱትን 17 አገራት በአንድ በማጠቃለል የሚደረገው የንግድ ለውውጥ የዓለምን 60 በመቶ አጠቃላይ ምርት መጠን  መድረስ እንደሚቻል ገልፀዋል ። ሚኒስትሯ አዲሱን የንግድ ፍኖተ ካርታ ባስተዋወቁበት ወቅት ከወጪ ንግዱ በተጨማሪም ቱርክ ከተመረጡት አገራት የምታስገባውን የምርት መጠንም ለመጨመር ዕቅድ እንዳላት ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here