ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በዓለም አቀፉ የከንቲባዎች ጉባኤ ላይ ሊሳተፉ ነው

0
815

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በዓለም አቀፉ ከንቲባዎች ጉባኤ ላይ ሊሳተፉ ነው

ዓለም አቀፉ የከንቲባዎች ጉባኤ ‹‹ሲ-40›› ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሀገን የሚካሔደውን ጉባኤ እንዲታደሙ ግብዣውን አቅርቧል፤ ምክትል ከንቲባውም እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በቀጣዩ ዓመት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1/2012 የሚካሔደው ጉባኤው የአባል አገራት ከተሞች ከንቲባዎች የሚገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማም በጉባኤው ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ጉባኤው በአየር ንብረት ለውጥና በካርቦን ልቀት ዙሪያ ሰፋ ያለ ሰዓት ወስዶ እንደሚወያይ የተነገረ ሲሆን ይህንም ተከትሎ የአየር ንብረት ባለሙያዎች፣ ዓለም አቀፍ  ተፅእኖ ፈጣሪዎች፣ ታላላቅ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

በየኹለት ዓመቱ የሚካሔደው እና በ1997 የተጀመረው ሲ-40 ባለፉት 12 ዓመታት ስድስት ጉባኤዎች የተካሔዱ ሲሆን በርካታ ዓለም አቀፋዊ ውሳኔዎችን ማሳለፍ የተቻሉባቸው ውጤታማ ጉባኤዎች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here