ዓለም አቀፍ የንግድ ልዑካን የአፍካን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ማዕከል በኢትዮጵያ ለመገንባት ዕቅድ እንዳላቸው አስታወቁ

0
559

ከተለያየ የዓለም ክፍል የተወጣጡ እና በተባበሩት መንግሥታት መሪነት አዲስ አበባ ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ የአፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።

ልዑካኑ ዛሬ ነሐሴ 30/2011 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የጎበኙ ሲሆን ከሚንስትር ዲኤታ ሲሳይ ቶላ ጋርም ተወያይተዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሕክምናው ዘርፍ ብሎም ወደ ሌሎች ዘርፎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ውይይት ተካሒዶበታል።

በውይይታቸው ወቅትም ከማዕከሉ ግንባታ ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ የሕክምና መሳሪያዎችንና መድኃኒቶችን ለማምረትም ተጨማሪ ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል። ሚንስትር ዲኤታውም ልዑካኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርጉት የትኛውንም ዓይነት ኢንቨስትመንት መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here