‹‹የልብ ጌጥ›› የቴሌቪዥን ድራማ በመቋረጡ ወደ ፍርድ ቤት አመራ

0
551

በደራሲ ይበልጣል ደረሰ ተጽፎ በትእግስት ይርጋ ፕሮዲውስ የተደረገው ‹‹የልብ ጌጥ›› የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በፕሮዲውሰሯና በቴሌቪዥን ጣቢያው ጄቲቪ ኢትዮጵያ አለመስማማት ምክንያት ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መድረሱን የድራማው ፕሮዳክሽን ማናጀር የሆኑት ጌቱ ግርማ ለአዲስ ማለዳ አረጋግጠዋል። ድራማው በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን እሁድ ከ7፡00 – 8፡00 ሰዓት ለስምንት ሳምንታት ሲተላለፍ ቆይቷል። ‹‹የልብ ጌጥ›› ወደ ፍርድ ቤት ከማምራቱ በፊት ጉዳዩን በሠላም ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ቢያደረግም አለመሳካቱን ጌቱ ተናግረዋል። ከቴሌቪዥን ጣቢያው ምንም ዓይነት ክፍያም እንዳልተፈፀላቸው አክለው ገልጸዋል።
የጄቲቭ የዋና ሥራ አስፈጻሚ የሕግ አማካሪ ለሆኑት ሹሜ የግጭቱን ምክንያትና ድራማው በቴሌቪዥን ጣቢያቸው መተላለፍ ለምን እንዳቆሞ ላቀረብንላቸው ጥያቄ “በዳኝነት ሥርዓቱ መፍትሔ ማግኘት የሚገባቸው ነጥቦች ለጋዜጣ ውይይት የማይቀርቡ በመሆናቸው፤ ፍ/ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ አስተያየት የለንም” በማለት መልሰዋል። እንዲሁም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመድረሱ በፊት ችግሩን ለመፍታት ያደረጉት ጥረት እንዳለ ለተነሳላቸው ጥያቄ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው ጄቲቪ እንዳልሆነ ገልጸው “ሁለቱ ወገኖች ያከናወኗቸው ማናቸውም ቅደመ ክርክር ወይም ድኅረ ፍርድ ውይይቶች ምን ጊዜም ምስጢራዊ ናቸው›› ብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here