‹‹የብርሃን ሽግግር›› እና ‹‹ዝማሬ ተዋህዶ›› የግጥም መድብሎችን በአንድ ላይ አስመረቁ

0
767

በዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ የተጻፉ የተሰኙ ሁለቱ የግጥም መድብሎች በብሔራዊ ቴያትር ህዳር 5 ቀን 2011 ተመረቁ ። የብርሃን ሽግግር የተሰኘው የግጥም መድብል ሙሉ በሙሉ ዓለማዊ ነገሮች ላይ በተለይ ደግሞ ፖለቲካው ላይ ያተኮረ ሲሆን በ55 ገጾች ተቀንብቦ የቀረበ ሲሆን በውስጡ 141 ግጥሞችን አካቷል። የብርሀን ሽግግር ደግሞ በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን ምዕራፍ አንድ ከፖለቲካው ለውጥ በፊት ያለውን፣ ምዕራፍ ሁለት ደግሞ ከፖለቲካው ለውጥ በኃላ ያሉ ሁነቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ዲያቆን መኩሪያ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ሌላው ለምርቃት የበቃውና በዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ የተጻፈው የግጥም መድብል ዝማሬ ተዋህዶ ይባላል። ዝማሬ ተዋህዶ ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። የግጥም መድብሉ በውስጡ 200 ግጥሞች የያዘ ሲሆን በ173 ገጾች ተዘጋጅቷል። ደራሲው መንፈሳዊ ግጥሞችን መጻፍ የጀመሩት ከ 18 ዓመት በፊት እንደሆነና እስከ አሁን ድረስ 1500 ግጥሞችን እንደጻፉ ገልጸዋል። በዝማሬ ተዋህዶ ውስጥ የተካተቱት ግጥሞችም ከ200ዎቹ ግጥሞች መካከል እንደሆኑ ተናግረዋል።
በግጥሞቹ ምርቃት ወቅት ደራሲ ይስማእከ ወርቁ የክብር እንግዳ የነበረ ቢሆንም ለህክምና ወደ ጀርመን በማምራቱ በዝግጅቱ ላይ ሳይገኝ ቀርቷል።
ዲያቆን መኩሪያ የግጥም መድብል ከማሳተማቸው በፊት ለድምጻዊያን መሀሙድ አህምድ፣ ለዛወርቅ አስፋውና አለም ከበደ ዝማሬ ሰርተው ለቤተክርስቲያን በስጦታነት ያበረከቱትን የመዝሙር ግጥሞች እንደሰጧቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም አቦነሽ አድነው ሁለተኛ የመዝሙር አልበሟን ግጥሞች መስራታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
ሁለተኛ የመዝሙር አልበሟን ግጥሞች መስራታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here