ዛሬ፤ ቅዳሜ ህዳር 8/2011 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የአሸናፊ ከበደ (ፕሮፌሰር) ሕይወትና ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት ይደረጋል፡፡
በዕለቱ የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬስብሐት የመነሻ ትንተና ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችና ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች እንደሚኖሩም ተገልጿል፡፡
ከዐሥራ አምስት ቀን በኋላ በሚኖረው ዝግጅት ላይ የሥነ ጥበብ ማዕከሉ በሥማቸው የተሰየመላቸው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ሥራዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም ከወዲሁ ታውቋል፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የብላቴን ጌታ ኅሩይ የልጅ ልጆችና ሌሎች እንግዶች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል በየ15 ቀኑ ቅዳሜ የጥበብ ዝግጅት ለሕዝብ ክፍት የሆነ ውይይት እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡