የውጭ አገራት ገንዘቦችን በሕገ ወጥ መንገድ ከሚመነዝሩ ግለሰቦች 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ተያዘ

0
496

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጳጉሜ 3/2011 የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ባካሔደው ፍተሻ 7 ሚሊዮን 608 ሽሕ የኢትዮጵያ ብር እና 53ሽሕ የአሜሪካን ዶላር ከሕገ ወጥ ገንዘብ መንዛሪዎች እጅ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎች የውጭ አገራት ዜጎች የሚኖሩባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት እና ቤት በመከራየት የሕገ ወጥ የገንዘብ መመንዘሩን ስራ ሲያከናውኑ እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ግልፅ አድርጓል። ድንገተኛ ፍተሻ በተካሔደበት ወቅት ተለያዩ አገራት መገበያያ ገንዘቦችን ከመቁጠሪያ ማሽን ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቀጣይም ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደሚያካሒድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here