ዳሰሳ ዘማለዳ ሰኞ ጳጉሜ 4/2011

0
961

1-የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ ገብተዋል።ጉብኝቱ የኹለቱን አገሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የልማት ትብብር እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።በዚሁ ጉብኝት  የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር  ለማ መገርሳ ከሩሲያ ወገን ጋር በሚደረግ ውይይት እንደሚሣተፉ ይጠበቃል። (ኤዜአ)

……………………………………………………….

2-ዓለማችን በ2050 ከወባ በሽታ ነጻ ልትሆን ትችላለች ተባለ። በሰው ልጆች ታሪክ ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረውና ሚሊየኖቸን የገደለው የወባ በሽታ በዚህ ትውልድ ዕድሜ ሊጠፋ እንደሚችል አንድ ጥናት ጠቆመ።በየዓመቱ 200 ሚሊዮን ሰዎች በወባ በሽታ የሚያዙ ሲሆን ብዙ ህጻናት ደግሞ በዚህ ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።(ቢቢሲ)

……………………………………………………….

3-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በ 2030 የአፍሪካ ብልጽግና ምልክት እንድትሆን የሚያስችላትን የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ይፋ አድርገዋል። በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ገጽታውን ለመለወጥ የተከናወኑትን ቁልፍ ክንውኖችን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ  ይህንን ለማሳካት የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።(አብመድ)

……………………………………………………….

4-አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ 87 የፌደራል ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚለቀቁ ተገለጸ። ከዚህ ውስጥ 367 ከቃሊቲ፣ 28 ከዝዋይ እና 439 ደግሞ ከሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ  ብርሃኑ ፀጋዬ ገልጸዋል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………………….

5-በቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕን በደረሰው አደጋ የሟቾች ማንነት ይፋ ሆነ።ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕን ከደረሰበት መከስከስ አደጋ ጋር ተያይዞ የሟቾች ማንነትን ለመለየት የተደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሒልተን ሆቴል ይፋ ባደረገው ምርመራ ውጤት የሰው ቅሪተ አካላትና አልባሳት 556 ሜትር ርቀት ተበታትነው የተገኑኙ ሲሆን የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎች 696 ሜትር ርቀት ተወርውረው ነው የተገኙት ተብሏል።(ኤዜአ)

……………………………………………………….

6-ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ ሳይገጠምላቸው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ያዘጋጀውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።ባለሃብቶች የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ መሳሪያውን በተሽከርካሪዎች ላይ አስገጥመው በማስገባት በተመጣጣኝ ክፍያ ደንበኞቻቸውን የሚያስከፍሉበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ መገባቱም አቶ ሙሴ ተናግረዋል።(ኤዜአ)

……………………………………………………….

7- የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ኅብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ  የዕርቅ ሳምንት አወጀ።የእርቅ ሳምንቱ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 22 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንዳስታወቁት፥ የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው ሰማይና ምድሩን በማስታረቅ በሰላምና በፍቅር የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ነው። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………

8- የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የ2011 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፈቃድ ሙሉ መረጃ ይፋ አድርጓል።መረጃው በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመዝግበው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚያገለግል መሆኑንም ነው ኤጀንሲው የገለፀው።(ዋልታ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here