በኬንያ የአይሲኦሎ ፍርድ ቤት አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ ቅጣት አስተላለፈ

0
1075

ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን የምትገኘው የአይሲኦሎ ግዛት ፍርድ ቤት ያለ ፈቃድ በኬንያ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ የእስር ቅጣት አስተላልፏል። ጥፋተኛ ናቸው የተባሉት ኢትዮጵያዊያን የተከሰሱበትን ጉዳይ ያመኑ ሲሆን ከቤተሰብ ጋር ለመኖር ወደ ኬንያ እንደገቡ እና ያለ ፈቃድ መግባት ይህን ያህል ከባድ አገራዊ ጉዳይ መሆኑን እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት የማርሳቤት ግዛት ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ በመኪና ሲጓዙ አይሲኦሎ ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊያን በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ኹለት ወራትን በእስር ቤት የሚቆዩ ሲሆን የእስር ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተወስኗል።

ነፃ የሰዎችን ዝውውር በሚመለከት የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከወራት በፊት ‹‹ማንኛውም ምስራቅ አፍሪካዊ ኬንያዊ ነው ፤ በሚኖርበት አገር መታወቂያ ፓስፖርት ሳያስፈልገው ወደ ኬንያ መግባትና መውጣት ይችላል›› ሲሉ በይፋ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here