በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ቁሳቁሶች ለበጎ አድራጎት ተሰጡ

0
609

የገቢዎች ሚኒስቴር በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ቀሳቁሶች በዕርዳታ አከፋፈለ።
ቁሳቁሶቹ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እና ለበጎ አድራጎት ማህበራት የተከፋፈሉ ሲሆን፣ በጎ አድራጎቱ ለአካል ጉዳተኞች፤ አረጋውያን፤ ሕፃናት እንዲሁም በሃገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አለመረጋጋቶች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ መሆኑ በልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ከነዚህም በተጨማሪ ከጎዳና ለተነሱ ሕፃናት፣ ለልብ ህሙማን እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፉ እንደሚደርስ ይጠበቃል። ድጋፉ ለምግብ እና ለአልባሳት ፍጆታ የሚውሉ ቁሳቁሶችን የያዘ ነው። በባለፈው በጀት ዓመት መንግስት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሚጠጉ ምርቶች በኮንትሮባንድ ሊገቡ ሲል ተይዟል።

ኮንትሮባንድ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች በገቢዎች ሚኒስቴር ሳይቀር የተለዩ ሲሆን ከክልሎች ሶማሌ፣ ኦሮሚያና በቤንሻንጉል ቀዳሚ ናቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here