የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመኖሪያ እና ለንግድ ሥራ የሚያገለግሉ ህንፃዎችን ሊገነባ ነው

0
783

ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመኖሪያ እና ለንግድ ሥራ የሚያገለግሉ ህንፃዎችን በአዲስ አበባ ሊያስገነባ ነው። ህንጻዎቹ የመኖሪያ እና የገበያ ማዕከል አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በአራት የተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ ይሆናል። ህንጻዎቹ ከአስር ፎቅ በላይ ሲሆኑ የንግድ ቤቶችንም አካተው በየካ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች ይገነባሉ፡፡

የዛሬ ዓመት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሦስት ዓመታት ውስጥ 16 ሺሕ ቤቶች መገንባት የሚያስችለውን ዕቅድ ለማሳካት የአፈር ምርመራ፣ የዲዛይን ክለሳና አዳዲስ ዲዛይኖች ከሚሠሩለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት መፈፀሙ ይታወሳል።

በወታደራዊው ደርግ መንግሥት በአዋጅ የተወረሱ ቤቶችን እንዲያስተዳድርና አዳዲስ ቤቶችን እንዲገነባ የተቋቋመው የቀድሞው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ በተለያዩ መዋቅሮች አልፎ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተብሎ ተቋቁሟል። የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጥራታቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለማልማት እና ለማስተዳደር የተቋቋመ መንግሥታዊ ድርጅት ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here