የአማራ ባንክ 2 መቶ ሚሊዮን ብር አክስዮን ሸጠ

0
828

በባህር ዳር ከተማ የአማራ ባንክን ለማቋቋም የሚያስችል የአክስዮን ሽያጭ ከተጀመረ ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ አክሲዮን እንደተሸጠ ታውቋል።

የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታ፣ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ ባንኩ የሚቋቋመው የአማራን ሕዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና ሀገራዊ ልማትን ለመደገፍ ነው። ዝቅተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ከ10 ሺህ ብር እንደሚጀምርና ይህም ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ30 በመቶ አክሲዮን ሊገዛ ደብዳቤ አስገብቷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን፣ የአክሲዮን ሽያጩ እንደተጠናቀቀ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃም ሀሰተኛ ነው ብለዋል።

የአክሲዮን ግዥ ጠያቂዎች ቁጥር በመጨመሩ ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ጋር በመተባበር ሽያጩን እስከ ቀበሌ ተደራሽ ከማድረግም ባለፈ የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭን እስከ ሦስት ወራት በማጠናቀቅ ወደ ታሰበው ዓላማ ለማስገባት እየተሠራ እንደሆነ ታውቋል።በባህር ዳር ከተማ የአማራ ባንክን ለማቋቋም የሚያስችል የአክስዮን ሽያጭ ከተጀመረ ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ አክሲዮን እንደተሸጠ ታውቋል።

የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታ፣ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ ባንኩ የሚቋቋመው የአማራን ሕዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና ሀገራዊ ልማትን ለመደገፍ ነው። ዝቅተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ከ10 ሺህ ብር እንደሚጀምርና ይህም ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ30 በመቶ አክሲዮን ሊገዛ ደብዳቤ አስገብቷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን፣ የአክሲዮን ሽያጩ እንደተጠናቀቀ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃም ሀሰተኛ ነው ብለዋል።

የአክሲዮን ግዥ ጠያቂዎች ቁጥር በመጨመሩ ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ጋር በመተባበር ሽያጩን እስከ ቀበሌ ተደራሽ ከማድረግም ባለፈ የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭን እስከ ሦስት ወራት በማጠናቀቅ ወደ ታሰበው ዓላማ ለማስገባት እየተሠራ እንደሆነ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here