ኮርፖሬሽኑ 11ኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በጅንካ ከተማ ሊከፍት ነው

0
1420

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) አስራ አንደኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ላይ ለመክፈት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑን አስታወቀ።

በኮርፖሬሽኑ ሥር ያሉ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እና የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩ 10 ዲስትሪክቶች ወደ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እንዲያድጉ የተደረጉ ሲሆን፣ ወደፊት በየአካባቢያቸው የውሀ፣ የመንገድ፣ የህንጻ እና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል። በተመሳሳይም በከተማዋ አንድ ቅ/ጽ/ቤት በመክፈት በአካባቢው ተመሳሳይ ሥራዎችን እንደያሚከናወኑም ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here