አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ

0
631

በተባበሩት መንግሥታት ልማት ፕሮግራም መሠረት የአገራትን ጤና አቅርቦት ለመለካት አንዱ መሣሪያ አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአፍሪካ እ.አአ. በ2012 ከነበረው 50.9 አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ በከፍተኛ ደራጃ አድጎ እ.አ.አ 2017 ወደ 54 ዓመት ደርሷል፡፡ ይህ አማካኝ ዕድሜ ጣሪያ መሻሻል የተመዘገበው ብዙኃኑ የአህጉሪቱ ሕዝብ በድህነት በሚማቅቅበት፣ የምግብ እጥረት ባለበት፣ መሃይምነት በተንሰራፋበት እና የሕክምና ተቋማት ዝቅተኛ ተደራሽነት ተከትሎ ተላላፊ በሽታና ንፁሕ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ዝቅተኛ በሆነበት ሁኔታ ነው፡፡ የታየው አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ መሻሻል ቢኖረውም አሁንም አህጉሪቱ ከሌሎች አህጉራት አንፃር በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የአህጉሪቷ ዝተቅኛው አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ ሆና የተመዘገበቸው ሴራሊዎን ከዓለምም ዝቅተኛው ደረጃን ይዛለች፡፡
ለአፍሪካ አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ መሻሻል ዋና ምክንያት አፍሪካ የምትታወቅባቸው የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ፣ ኤችአይ ቪ፣ የሆድ በሽታ ጨምሮ በአስር ዋነኛ የጤና ሥጋቶች ሰበብ የሚሞተው ሕዝብ ቁጥር መቀነሱ ነው፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት መሠረት ይህም የሆነው የልዩ የጤና መርሓ ግብሮች ተግባራዊ መደረጋቸው ነው፡፡ ከአፍሪካ አገራት አልጄሪያ ቀዳሚውን አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ ስትይዝ ኢትዮጵያ በበኩሏ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም አሰገራሚ የሆነ አማካኝ የዕድሜ ጣራን መሻሻል ካመጡ አገራት መካከል የምትመደብ ሲሆን እ.አ.አ. 2000 ከነበረው 50.9 አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ ተስፈንጥራ በያዝነው ዓመት 2018 ላይ 65.9 መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ልማት ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here