ሰሞነኛ

0
506

‹‹አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ፣ ሜቴክ እንዳያየው ሳያርፍ ተመለሰ››

ይህን ሰሞነኛ ቀልድ በማህበራዊ የመገናኛ አውታር በተለይም ፌስቡክ ብዙዎች ሲቀባበሉት ሰንብቷል፡፡
መነሻውም የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በብርታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስለተፈፀመ የሙስና ወንጀል የሰጠው መግለጫ ነው፡፡ በመግለጫውም ሜቴክ ከ2004 እስከ 2010 ድረስ ብቻ ከውጭ አገራት ኩባንያዎች ያለምንም ጨረታ የ37 ቢሊዮን ብር ግዥ እንደፈጸመ መነገሩ ይታወሳል፡፡ ከግዥው ውስጥም ከአንድ የእስራኤል ኩባንያ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙና ከ50 ዓመት በላይ ያገለገለገሉት አውሮፕላኖች ይገኙበታል፡፡ ግዥው የተፈጸመው አገራዊ ፕሮጀክቶችን በአውሮፕላን እየተንቀሰቀሱ ለመከታታል በሚል ይሁን እንጂ እስካሁን አንዱ አውሮፕላን የት እንዳለ እንደማይታወቅ ነው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ያመለከተው፡፡ ይህን የሰሙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ሰሞኑን ‹‹አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ፣ ሜቴክ እንዳያየው ሳያርፍ ተመለሰ›› የሚል ስንኝን ሲቀባበሉ ተስተውለዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here