በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልግ ግብፅ አስታወቀች

0
924

ግብፅ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ እና ተያያዥ በሆኑ የናይል ተፋሰስ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ከግብፅ በሰተቀረ ሌላ የውጭ አካል ጣልቃ ገብነት እና የራሳቸውን ሀሳብ ማንፀበራቅ  እንደማያስፈልግ አስታወቀች። አያይዛም በሦስቱ ባለድርሻ አገራት ላይም ምንም አይነት ምክር ወይም ጫና ማሳደር እንደማይችሉ አስታውቃለች።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ከፈረንሳዩ አቻቸው ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በሚመለከት በቀጣይ በሱዳን ካርቱም የሚደረገው ውይይት ውጤታማ እንደሚሆንና ጠንካራ ውሳኔዎችም ይሰሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል። ሳሜህ አያይዘውም በግድቡ ዙሪያ መግባባት ላይ ያልተደሰባቸው ጉዳዮች በቴክኒካዊ ጉዳዮች እንጂ ምንም አይነት የፖለቲካ ጉዳይ ወይም የፖለቲካ አለመግባባት ተደርገው መቆጠር እንደሌለባቸውም  በግልፅ አስታውቀዋል።

ሚንስትሩ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ግን አሁንም አደራዳሪዎችን እና አሸማጋዮችን መጋበዝ ፍላጎታቸው እነደሆነ የግብፅን አቋም አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here