ከ 3 መቶ በላይ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄዎቻቸውን አቀረቡ

0
720

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ እና አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ያቀረበውን የመጀመሪያውን ዙር የስራ ምክረ ሃሳብ (ፕሮጀክት ፕሮፖዛል) ጥሪ ተከትሎ ሦስት መቶ የሚሆኑት ፕሮፖዛሎቻቸውን አቅርበው የገንዘብ ድጋፍ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ኮምኒኬሽን ኃላፊ ሀና አጥናፉ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት የቀረቡት የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ከተጠበቀው በላይ ቁጥራቸው ከፍ ያለ እንደሆነና ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚታየው አንገብጋቢው ድህነት  ትረስት ፈንዱ የሚያደርገው ጥረት በሀገር ውስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ሁሉ የተጠናከረ ድጋፍ እና ርብርብ እንደሚያስፈልገው በማያወላዳ ሁኔታ የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከተመሰረት አንድ አመት ያስቆጠረው ትረስት ፈንዱ በሰባ ሰባት አገራት ውስጥ ከሚገኙ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት ካሰባሰበው ብር ውስጥ ከአንድ መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ አንገብጋቢ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here