ዳሰሳ ዘማለዳ ረቡዕ መስከረም 7/2012

0
693
  • ለስሚንቶ ፋብሪካዎች ግብዓት የሚያመርተው አባይ ኢንዱስትሪያል ልማት አክሲዮን ማኅበር በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሦስት ከፍተኛ ፈቃዶች ተሰጡት። ድርጅቱ በአማራ ክልል ደጀን ለሚገነባው አባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓቶችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………….

  • የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት/ኢጋድ/ ኹለተኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ስብሰባውም በዋናነት በቀጠናው አገራት ያለውን የስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ በተደረሰው የናይሮቢ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ሲሆን ስደተኞችን መንከባከብ፣ ስደተኞች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በማስቀረትና ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የሚያደርግ ነው።(ዋልታ)

…………………………………………..

  • በኢትዮጵያ አጠቃላይ የጤና ዘርፍ ወጪ በ2006 ከነበረው 49 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በ2009  ወደ 72 ቢሊየን ብር ከፍ ማለቱን በ7ኛው ብሄራዊ የጤና ወጪ ስሌት የጥናት ውጤት ላይ ይፋ ተደርጓል።ለህክምና ከታካሚዎች ኪስ የሚወጣ ውጪ ደግሞ ከ33 በመቶ ወደ 31 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፥ ከመንግስት የሚወጣው ወጪ ደግሞ ከ30 በመቶ ወደ 32 በመቶ ከፍ ብሏል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………….

  • “ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢንሼቲቭ” በረሀማነትን ለመከላከል 8ሺሕ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ደን በሳህል ቀጣና ለመትከል ያለመ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።4 ቢሊዮን ዶላር የተመደበለት ፕሮጀክቱ ከ12 አመታት ቆይታ በኃላ ለማሳካት የተቻለው 15 በመቶ የሚሆነዉ መፈፀሙን አስታዉቋል።እ.ኤ.አ በ2007 የተጀመረ ሲሆን ዓላማውም የሰሃራ በረሃ መስፋፋትን ለመከላከል እና በቀጠናው የሚገኙ ድሃ ሀገራትን ኢኮኖሚ ለማሻሻል ነው።(ኤዜአ)

………………………………………………….

  • በባህር ዳር ከተማ በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ነገ ሐሙስ መስከረም 8/2012 ይጀመራል። (አብመድ)

……………………………………………………..

  • በባሕር ዳር ከተማ ዛሬ ጣና ክፍለ ከተማ በ20 ጆንያዎች የተቋጠረ 497 ሽጉጥ እና ወደ 46 ሺህ የሚገመት ጥይት  በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ (ዋልታ)

……………………………………………………….

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ:: የኮሚቴረ አባላት ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረገው የፅዳት መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጎን መቆማቸውን እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። (አዲስ ቲቪ)

………………………………………….

  • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ማኅበር ተወካዮችን አነጋገሩ፡፡ አባላቱ ያካበቱት ልምድ በቀጣይ አገራዊ ጥቅም ላይ ሊውል በሚችልበት ዙሪያም ተነጋግረዋል። (አዲስ ቲቪ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here