ዳሰሳ ዘማለዳ ሐሙስ መስከረም 8/2012

0
565
  • የአርሜኒያ መንግሥት ትናንት ረቡዕ መስከረም 7/2012 በኢትዮጵያ ኢምባሲውን ለመክፈት መወሰኑን ይፋ አድርጓል። የኢምባሲው መከፈት በኹለቱ አገራት የሚኖረውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያጠናክራል ሲሉ የአርሜኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዞርሃብ ማናስካኒያ ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

  • መቀመጫው በግብፅ የሆነ እና ባለ ኹለት እንዲሁም ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ የመጓጓዣ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሆነ አስታወቀ። ስራውንም እስከ ፈረንጆቹ 2019 መጨረሻ ድረስ እንደሚጀምር ተናግሯል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………….

  • ‹‹የንፋስ ፍልሚያ›› የተሰኘው አማረኛ ፊልም ለ92ኛው የኦስካር ሽልማት ለመወዳደር ወደ አሜሪካ አቅንቷል። በምርጥ ዓለም አቀፍ ፊልም ዘርፍም እንደሚወዳደር ታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………

  • በትናንታው ዕለት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 19 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። አደንዛዥ ዕፁ ከብራዚል ሳኦ ፖሎ እንደመጣ ተነግሯል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………..

  • በአማራ ክልል ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ቅርሶችን ለመንከባከብና ከጉዳት ለመጠበቅ በዚህ ዓመት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተቀርፆ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን 40 ሚሊዮን ብርም ለመሰብሰብ ታቅዷል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………

  • በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የሰዎችን ህይወት አጥፍተዋል ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 156 ደረሰ። (ሸገር)

……………………………………………………………

  • ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ብራንድ ባላቸው የሆቴሎች ሰንሰለት መገኛ በሚል ከዐስር የአፍሪካ አገራት በአምስተኛ ደረጃ ላይ መገኘቷ ተዘግቧል። (አዲስ ቲቪ)

……………………………………………………

  • በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ594 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆስፒታል ግንባታ ሊካሔድ ነው። ሆስፒታሉ በ8ሽሕ ካሬ ላይ የሚያርፍ ሲሆን የጊቢው ስፋትም 11 ሔክታር ይሆናል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here