የካፋ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን አፀደቀ

0
594

የካፋ ዞን ምክር ቤት ባሰለፍነው ሐሙስ ኅዳር 6 ቀን 2011 የብሔረሰቡን የክልልነት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
የካፋ ዞን የቡና መገኛ መሆኑን ዕውቅና ከመስጠት ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ የዞኑ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ባሰሙበት ወቅት ክልል የመሆን ጥያቄ መስተጋባቱ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ተንሸራሽሯል፡፡
ከሳምንታት በፊት የክልሉ ምክርቤት የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን ማፅደቁን እና ለሕዝበ ውሳኔ መምራቱ ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ዞኖች የክልልነት ጥያቄ እየቀረበ ይገኛል፡፡ ከሳምንት በፊት የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ላይ የዞኑ ምክር ቤት ውይይት አድርጎ የጥያቄውን አግባብነት ከተቀበለ በኋላ በጉዳዩ ላይ ኅብረተሰብ እንዲወያይበት በሚል ለዞኑ መስተዳደር ምክር ቤት (ካቢኔ) መምራቱም ይታወሳል፡፡
ክልል የመሆን ጥያቄ ተፈፃነት የሚያገኘው ጥያቄው ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ሕዝበ ውሳኔ ሲሰጥበት ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here