መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 ለሰሃራ በታች ላሉ አገራት የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ያደረጉ ባንኮች

10 ለሰሃራ በታች ላሉ አገራት የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ያደረጉ ባንኮች

ምንጭ፡-ኳርትዝ አፍሪካ (2022)

ቻይና የአፍሪካ የቅርብ ወዳጅ ከሆነች ከራርማለች። ይህንን ተከትሎም በአፍሪካ የአኅጉሪቱን የከተማ ማስፋፋት ሥራ ብቻዋን በሚባል ደረጃ ተቆጣጥራ ይዛዋለች። በአውሮፓውያን ዘመን ቀመር መሠረት ከ2007 እስከ 2020 በነበሩት ዓመታት፣ በቻይና ሁለት የውጭ አገር ልማት ባንኮች 20 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በአፍሪካ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ፈሰስ አድርገዋል። ይህም ብቻ የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች ስምንት ባንኮችና ትብብሮች ካደረጉት ፈሰስ ድምር የሚበልጥ ነው።
ታድያ የቻይና የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት የጎንዩሽ ጉዳቶች ቢኖሩትም፣ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ቀላል የማይባል ጥቅምን አስገኝቷል።

ኳርትዝ አፍሪካ ባስቀመጠው በዚህ ዐስርቱ ዝርዝር እንደሚታየው፣ በተደጋጋሚ ሥሙ ሲጠቀስ የሚሰማው የዓለም ባንክ በ0.9 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ በማድረግ በዐስረኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። በዚሁ ዘገባ መሠረት ደግሞ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ስበት የነበረው የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ሲሆን፣ ትራንስፖርት እና ነዳጅ ደግሞ ቀጥለው በቅደም ተከተል ይገኛሉ።


ቅጽ 4 ቁጥር 187 ግንቦት 27 2014

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች